ለቅሶህን አልቅሼ ቀብርህንም ባይም አባዬ ሞትህን አልተቀበልኩትም ቤተሰብ ሰብሳቢ ለሁሉም አለሁ ባይ የሁሉ ተጠሪ የሁሉ ተወካይ መውጣቱ መውረዱ ከብዶህ ነበረ ወይ አንተ ስራ አፍቃሪ እረፍት የማትወደው ይመስክር ቤታችን ጣሪያና ግድግዳው የሌለበት የለም እጅህ ያልነካካው ሁሉንም አክባሪ ወገንን ሰብሳቢ መከታ ቤታችን ሁሌም ቅን አሳቢ እባክህ ንገሪኝ ቃል ይውጣ ከአፍህ ምነው በመጦሪያህ ለምን በማረፊያህ ከልካይ የለሹ ሞት ስለምን ወሰደ ሰላምና ደስታን ፍቅርን ለሰጠኸኝ ሳጠፋ ታግሰህ ስሳሳት ለቻልከኝ በህይወቴ ሁሉ ደስተኛ ያረከኝ ውለታ ሳልመልስ ስለተለየኸኝ ውስጤ ተቃጠለ በጣም ተቆጨሁኝ ትሁት ሰው አፍቃሪ ሁሉንም አክባሪ ብትሆን ተጠራህ ምቹ ለፈጣሪ መልካምነትህን ቢመሠክርም ሰው ቸሩ መድሀኒዓለም ነፍስህን ይማረው።